ዛሬ ኢትዮ ቴሌኮምን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ለመምራት ኃላፊነታቸውን የተረከቡትን ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩን እናስተዋውቃችሁ፡፡
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በኢንፎርሜሽን ሲስተም በመጀመርያ ዲግሪ ተመርቀዋል፣ እንግሊዝ ከሚገኘው ኦፕን ዩኒቨርሲቲ ደግሞ በቢዝነስ አድሚኒስትሬሽን የማስተርስ ዲግሪ አግኝተዋል፡፡ አዲሷ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በቴሌኮም ዘርፍ ለስምንት ዓመታት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂውን ከመምራት አንስቶ፣ እስከ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚነት ድረስ ማገልገላቸውን ከኢትዮ ቴሌኮም ሕዝብ ግንኙነት ክፍል የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡
የኢትዮ ቴሌኮም የሥራ አመራር ቦርድ አባል፣ በግሉ ዘርፍ የዶክሳ አይቲ ቴክኖሎጂ ኩባንያ መሥራችና ማኔጂንግ ዳይሬክተር፣ በተጨማሪም አዳዲስ ኩባንያዎችን በማቋቋምና ወደ ሥራ በማስገባት አገልግሎት መስጠታቸው ታውቋል፡፡