EducationEthiopiaPolitics

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ ምክንያት ከስራ የተባረሩ 42 መምህራንን ወደ ስራ እንዲመለሱ ውሳኔ አስተላለፉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከ50 የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከተዉጣጡ 3 ሺ 175 መምህራን ጋር እየተወያዩ ነው፡፡ጠቅላይ ሚኒስትሩ
እውቀት እና የአካዳሚክ ነጻነት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ ለሚኖር ነጻ አስተሳሰብ ቅድመ ሁኔታዎች መሆናቸውን ተናግረዋል።
ዶክተር አብይ ለመምህራኖቹ ጥያቄ በሰጡት ምላሽ በትምህርቱ ዘርፍ የተያዘውን ግብ ለማሳካትም ብቁ መምህራን እና ጥራት ያለው ትምህርት አስፈላጊ መሆኑን ገልጸዋል።
ብቃት ሳይኖርና ያለ ዕውቀት ማስተማር ብክነት እና ኢ – ፍትሃዊነት ነዉ ብለዋል፡፡ከዚህ አንጻርም በዘርፉ ማሻሻያዎችን ማድረግ ቁልፉ ጉዳይ መሆኑን ጠቅሰዋል።
የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጥላዬ ጌቴ ከዚህ ቀደም ተገቢ ባልሆነ መንገድ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተባረው የነበሩት መምህራን ይቅርታ ተደርጎላቸው ወደ ስራቸው እንዲመለሱ በጠየቁት መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲመለሱ ወስነዋል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami