የሐገር አቀፍ ትምህርት ፈተናዎች እና ምዘና ኤጀንሲ በስሜ በሀሰት የተከፈቱ የተለያዩ የፌስ ቡክ ፔጆች የ12ኛ ክፍል ፈተና ወጥቷል፡፡ በሚል ያስወሩት ወሬ ሀሰት ነዉ ብሏል፡፡ ኤጀንሲዉ አስከ ሀምሌ 25 ግን የፈተናዉ ዉጤት ይፋ እንደሚሆን ለአርትስ ቲቪ ተናግሯል፡፡
በኤጀንሲዉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ረዲ ሾና ለጣቢያችን ፈተናዉ ገና በእርማት ላይ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የሀገር አቀፍ ትምህርት ፈተናዎች እና ምዘና ኤጀንሲ ትክክለኛዉ የፌስቡክ ገጽ 79 ሺ ተከታዮችና 78 ሺ ላይክ ያለዉ ሲሆን፤ የኤጀንሲዉን ሙሉ ስም www.neaea.gov.et በመጻፍ ወደ ድረ ገፁ በመግባት መረጃዎችን ማግኘት ይቻላል ብለዋል፡፡