የጎንደሩ ፋሲል ግንብ እንደያኔዉ ዘመን ህያዉ ሊሆን ነዉ ተባለ፡፡
እንዴት አትሉም?
ከፋሲል ግንብ ሲደርሱ ከእንግዲህ ግንቡን ብቻ አትጎበኙም ፤የያኔዉን ዘመን ስልጣኔ ታሪክ ህያዉ ሆኖ ታዩታላችሁ ተብላችኋል፡፡
በግብሩ ቦታ ግብር ይካሄዳል፣ ፍሪዳዉ ይቆረጣል፣ጠጁም ይጣላል፤ እርሶዎም በብርሌዉ ጠጆዎን እየኮመኮሙ የያኔዉን የጎንደር ታሪክ ተጋሪ ይሆናሉ፡፡
በመዋኛዉ ገንዳም፣በአዝማሪዎቹ መቀመጫም ፣ በፈረሶቹ መቆሚያም ፣ሁሉም እንደዚያኛዉ ዘመን ይሆናል፡፡
የኢትዮጵያ ቱሪዝም ድርጅት ምክትል ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ሰርፀፍሬ ስብሀት ትላንት በጎንደርን ፍለጋ የጉዞ ማስታወሻ መጽሀፍ ምረቃ ላይ እንደተናገሩት የጎንደር ፋሲል ግንብ ቱሪስቶችን የበለጠ እንዲስብ ህያዉ የማድረግ እቅድ ተይዟል፡፡