የደቡብ ብሄር ብሄረሰቦች ህዝቦች ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሚሊዮን ማቲዎስ ለጋዜጠኞች በሰጡት መግለጫ እንደተናገሩት በሀዋሳ በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ከ 1 ወር በላይ የቆዩ ተፈናቃዮች ከዛሬ ጀምሮ ወደ የቀያቸዉ ይመለሳሉ ብለዋል፡፡
አቶ ሚሊዩን ተፈናቃዮቹ የሚመለሱባቸዉ መንደሮች የቀድሞ ሰላማቸዉን ማግኘታቸዉን ተናግረዋል፡፡
ተፈናቃዮቹ እስኪቋቋሙ ድረስ ቤተሰብ ላላቸው በወር 4 ሺ ብር ፤ቤተሰብ ለሌላቸው ደግሞ በወር 2 ሺ ለሶስት ወር የቤት ኪራይ የሚሆናቸውና እንዲሁም ለሁሉም ለተፈናቀሉ ዜጎች የአንድ ወር ቀለብ ወጪ በመንግስት ተሸፍኖላቸዋል፡፡
በግል ቤታቸው ይኖሩ የነበሩና ቤታቸው የተጎዳባቸው ዜጎች ቤታቸውን ለመጠገን የሚያስችል ወጪ ተሰልቶ እንዲከፈላቸውም መደረጉንም ሰምተናል፡፡