በናይጀሪያ የህገ ወጥ ሰዎች ዝውውርን ለመቆጣጠር የተቋቋመ ኤጀንሲ አንድ ችግሩን ለመከላከል የሚያግዝ ቴክኖሎጂ ይፋ ማድረጉ ተሰምቷል፡፡
ቴክኖሎጂው አይ ሪፖርት በመባል ይታወቃል፡፡ ሰዎች ባሉበት ሆነው ወንጀል ሲፈጸም ካዩ ለማዕከሉ ሪፖርት ማድረግ የሚያስችል በኢንተርኔት አማካይነት የሚሰራ መተግበሪያ ነው፡፡
እናም ማንኛውም ናይጄሪያዊ ሰዎችን በህገወጥ መንገድ የሚያዘዋውሩ ግለሰቦችን በሚያይበት ወቅት ይሄን መተግበሪያ በመጠቀም ጉዳዩን ለሚመሩት ባለስልጣናት የማንቂያ መልእክት በመላክ ተጠቂዎችን ለመታደግ ይችላል ተብሏል፡፡
ናይጄሪያ ህገወጥ የሰዎች ዝውውር ከሚፈፀምባቸው የአፍሪካ ሀገራት ቀዳሚዋ ናት፡፡ በፈረንጆቹ 2016 ብቻ 14 ሺህ ዜጎቿ የችግሩ ሰለባ መሆናቸው ተነግሯል፡፡
ዘገባው የሲ ኤን ኤን ነው፡፡