በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኢምባሲ የመጀመርያ ዲግሪ ላላቸው ኢትዮጵያውያን ነፃ ትምህርት ዕድል ሊሰጥ ነው፡፡
በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኤምባሲ የመጀመርያ ዲግሪ ላላቸው ኢትዮጵያውን ነጻ የትምህርት ዕድል እንደሚሰጥ በኢትዮጵያ የእንግሊዝ ኢምባሲ ከፍተኛ የፖለቲካ ባለሙያ ጀሚ ኦርተን ገልጸዋል፡፡
ጀሚ ኦርተን ከአማራ ብዙኃን መገናኛ ጋር ባደረጉት ቆይታ የእድሉ ተጠቃሚ የሚሆኑት ተማሪዎች በማንኛውም የትምህርት ዘርፍ የመጀመርያ ዲግሪ ያላቸው አምልካቾች መሆኑን አስታውቀዋል፡፡
አመልካቾች ሁለት ዓመት የስራ ልምድ ያላቸውና ኤምባሲው በሚሰጠው የእንግሊዝኛ ቋንቋ ፈተና አጥጋቢ ውጤት ማምጣት የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
በመጭው መስከረም 13 ተማሪዎች የነፃ ትምህርት እድል ተጠቃሚ ይሆናሉ ፡፡
መስፈርቱን የሚያሟሉ ሁሉ በእንግሊዝ ሀገር በሚገኙ ዩኒቨረሰቲዎች በፍላጎታቸው ይመደባሉ ሲሉ ገልፀዋል፡፡
እንግሊዝ ባለፉት አምስት ዓመታት ከ2መቶ በላይ ኢትዮጵያውያን አመልካቾችን አስተምራለች፡፡
ለበለጠ መረጃ www.chevening.org ይጠቀሙ፡፡