EconomyEthiopia

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የጅማ ኢንደስትሪ ፓርክ ጎበኙ፡፡

ከጅማ ኢንደስትሪ ፓርክ በተጨማሪ ዱከም ኢንዱስትሪያል ፓርክን ጨምሮ በጅማና በቦንጋ የሚገኙ የጫካ ቡናዎችን ጎብኝተዋል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በግንባታ ላይ የሚገኘውን የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ ከተባበሩት ዓረብ ኢሚሬቶች ከመጡ ባለሀብቶች ጋር መጎብኘታቸውን የጅማ ከተማ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት አስታውቋል።
በጉብኝቱ ወቅትም ባለሀብቶቹ በኢንዱስትሪ ፓርኩ ውስጥ የመሰማራት ፍላጎት ማሳየታቸውንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።
በ61 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በጅማ ከተማ በመገንባት ላይ የሚገኘው የጅማ ኢንዱስትሪ ፓርክ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ከ93 በመቶ በላይ መከናወኑንም አስታውቋል።
የፓርኩ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንታባ ዘጠኝ ሼዶችን ጨምሮ አስፈላጊ የሆኑ መሰረተ ልማቶች የተሟሉለት መሆኑንም ጽህፈት ቤቱ ገልጿል።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami