ዥንዋ እንደዘገበው ተማሪዎቹ በማህበራዊ እና በተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዘርፎች የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞችን የሚከታተሉ ሲሆኑ ከ29 ተማሪዎች ውስጥ የዶክትሬት ዲግሪ ተማሪዎችም ይገኙበታል፡፡
የትምህርት ሚኒስትር ዲኤታ ዶክተር ሳሙኤል ክፍሌ የቻይና መንግስት ለኢትዮጵያዉያን የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የሰጠው ነፃ እድል በሁለቱ ሃገራት መካከል ያለውን ጠንካራ የዲፕሎማሲ፣ የባህል እና የምጣኔ ሃብት ትስስር ያመለክታል ብለዋል፡፡
በሃገሪቱ የወደፊት እጣ ፋንታ ላይም ወሳኝነት ያለው የተማረ የሰው ሃይል አጋዥ ስለሆነ የሁለቱን ሃገራት ግንኙነት አጠናክረን እናስቀጥላለን ነው ያሉት ዶክተር ሳሙኤል፡፡
በኢትዮጵያ የቻይና አምባሳደር ታን ጄን ትምህርት ለአንድ ሃገር እድገት ትርጉም አለው፤ቻይና ለአፍሪካውያን የምታደርገውን የትምህርት ድጋፍ አጠናክራ ትቀጥላለች ብለዋል፡፡
የትምህርት እድል ተጠቃሚ ተማሪዎቹ በትምህርት ከሚያገኙት እውቀት በተጨማሪ የሁለቱን ሃገራት የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት እንደሚያጠናክርም አምባሳደር ጄን ገልፀዋል፡፡