ባንኩ በጋዛ የሚገኙ የፍልስጤም ወጣቶች የስራ ዕድል የሚፈጥር አዲስ ፕጀክት ይፋ አድርጓል፡፡
ለፕሮጀክቱ 17 ሚሊዮን ዶላር የተመደበ ሲሆን በዚሁ ፕሮጀክት ከ400 ሺህ በላይ ወጣቶች ተጠቃሚ የሆናሉ ነው የተባለው፡፡
ወጣቶቹ ወደ ስራው ከመግባታቸው በፊት የክህሎት ስልጠናዎችን እንዲያገኙ የሚደረግ ሲሆን ተቀጥረው ከመስራት ባሻገር የራሳቸውን ገቢ የሚያገኙበት የስራ ዓይነትም ይመቻችላቸዋል፡፡
ፕሮጀክቱ በዋናነት መንግስታዊ ካልሆኑ ድርጅቶች ጋር በመተባበር የሚሰራ እንደሆነ የፍልስጤም የኢንፎርሜሽን ማዕከል ተናግሯል፡፡