ይህ የተባለው ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ እና የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ሀላፊው ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ ዛሬ በዓሉን አስመልክቶ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው፡፡
በዓሉን አቅመ ደካሞችን በመደገፍ፣ችግኝ በመትከል፣የአረጋዊያንን ቤት በማደስ፣ከተማዋን በማፅዳት እና የተለያዩ የበጎፍቃድ ስራዎችን በማከናወን ለማክበር ቅድመ ዝግጅቶች መጠናቀቃቸው ነው በመግለጫው የተነገረው ።
የከተማዋ ወጣቶችም በዚህ በጎ ስራ ላይ ተሳታፊ እንዲሆኑ ጥሪ ቀርቧል ሲል የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህፈት ቤት በድረ ገፁ ላይ አስፍሯል፡፡