የውይይት መድረኩ የፊታችን እሑድ ነሐሴ 13 ቀን ይካሔዳል፡፡
በትግራይ ክልል የፖሊሲ ጥናት ተቋም ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ፍሰሃ ሀብተ ፂዮን እንደተናገሩት የውይይት መድረኩ የመለስ ዜናዊ ስራዎች ላይ የሚያተኩር ሲሆን የሃገሪቱ የህዳሴ ጉዞ እንዲሁም ወቅታዊ ሁኔታዎች ይዳሰሱበታል፡፡
የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን በድረ ገጹ እንዳስታወቀዉ ዶ/ር ፍሰሀ በመድረኩ ነባር እና አዲስ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ምሁራን፣ፖለቲከኞች፣የተለያዩ ድርጅት ተወካዮች እነዲሁም የመቀሌ ከተማ እና አካባቢው ነዋሪዎች የሚሳተፉበት ሲሆን 2000 ሰው እንደሚገኝ ይጠበቃል ብለዋል፡