አዴኃንና የአማራ ክልል መንግስት የአማራን ህዝብ ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ የዉይይታቸዉ ሀሳብ ነዉ፡፡
አዴኃን ወደ ሀገሩ ገብቶ በሰላም እንዲንቀሳቀስና ጥሩ አጋር ሆኖ እንዲሰራ የክልሉ መንግስት ድጋፍ እንደሚያደርግለትም ገልጧል ልዑኩ፡፡ የልኡኩ አባል የአማራ ክልል መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ ንጉሱ ጥላሁን የኤርትራ መንግስት ጉዳዩ እልባት እንዲያገኝ ያሳየውን አጋርነት ማድነቃቸዉን የአማራ መገናኛ ብዙሃን ዘግቧል፡፡
የኤርትራ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኡስማን ሳሌህ ‹‹የኤርትራ መንግስት የሰላም ድርድሩን ይደግፋል፤በኤርትራ የሚገኙ ነፍጥ ያነሱ የፖለቲካ ድርጅቶችም ወደ ኢትዮጵያ ገብተው በሰላም እንዲታገሉ ሀገራችን ትሰራለች›› ብለዋል፡፡
ኢዴኃን ራሱን ለድርድር ዝግጁ በማድረጉ እና የአማራ ክልል መንግስትም ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠቱ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ኡስማን ሳሌህ፡፡