በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ የ8 ሰዎች ህይወት ማለፉን ፋና ዘግቧል።
ጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው፥ አደጋው የደረሰው ነሃሴ ነሀሴ 8 ቀን 2010 ዓ.ም ከሌሊቱ 7 ሰዓት አካባቢ ነው።
በመሬት መንሸራተት አደጋውም የ8 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ ስድስቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ሲሆኑ፥ ሁለቱ ደግሞ ስራ ለማገዝ ከሌላ ቦታ ወደ ስፍራው ያቀኑ ናቸው።
በአደጋው ከሰው ህይወት በተጨማሪ ቤት ከነሙሉ ንብረት፣ በአካባቢው የተዘራ ሰብል፣ አትክልትና ፍራፍሬ በሙሉ መውደሙም ተገልጿል።