EthiopiaSocial

በአዲስ አበባ ለሚገኙ የጎዳና ተዳዳሪዎች ዛሬ ነፃ የህክምና አገልግሎት ይሰጣል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ከዘመን እና ሞጋቾች ድራማ ጋር በመሆን ፥ ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት እስከ ሌሊቱ 6 ሰዓት ድረስ በመዲናዋ ጎዳና ላይ የሚገኙ ሰዎች የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋሉ።
የበጎ ፈቃድ አገልግሎቱ ወር በገባ በ16ኛው ቀን በቀጣይነት እንደሚሰጥ እና ወደ ሌሎች ከተሞችም ለማስፋት መታቀዱን የዘመን ድራማ ደራሲ አቶ መስፍን ጌታቸው ተናግረዋል።
ሰኔ 16 ቀን በአዲስ አበባ የተካሄደውን የመደመር ህዝባዊ ሰልፍ ታሳቢ በማድረግ በየወሩ የተለያዩ የበጎ ፈቃድ ስራዎች እየተሰሩ እንደሚቀጥሉም ሰምተናል።
በጤና ጥበቃ ሚኒስቴር የህክምና አገልግሎት ዳይሬክተር ጀኔራል ዶክተር ዳንኤል ገብረሚካኤል፥ የተለያየ አገልግሎት የሚሰጡ አምስት የጤና ባለሙያዎች ቡድን ከአርቲስቶች ጋር በመሆን ይሰራል ብለዋል።
ለአገልግሎቱ መስጫም 3 ተንቀሳቃሽ ክሊኒክ እና 2 ተንቀሳቃሽ ድንኳን ተዘጋጅቷል ።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami