በዚህ ሳምንትም በክፍለከተማ ደረጃ ያሉ ዋና ዋና አመራሮች እንደ አዲስ እንደሚዋቀሩ የአዲስ አበባ ከንቲባ ፅህፈት ቤት በድህረ ገፁ አስታዉቋል፡፡
የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ በወቅታዊ የከተማዋ ጉዳዮች ላይ በሰጡት መግለጫ
የተጀመረውን ህብረተሰቡን ተጠቃሚ የማድረግ እና አሁን እየታየ ያለውን ሀገራዊ ተስፋ ለማደናቀፍ እንዲሁም የመዲናችንን ሰላም ለማደፍረስ ሙከራዎች እየተደረጉ መሆኑን የሚያሳዩ ምልክቶች እየታዩ በመሆኑ ህብረተሰቡ ከአስተዳደሩ ጎን በመቆም ድርጊቱን እንዲከላከል ጠይቀዋል።
በተጨማሪም ሰሞኑን በርካታ ህገወጥ መሳሪያ ሲዘዋወር በህብረተሰቡ ጥቆማ በቁጥጥር ስር መዋሉን ያስታወሱት ወ/ሮ ዳግማዊት በቀጣይ ነዋሪው የሚያያቸውን አጠራጣሪ ነገሮች ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት እንዲተባበር ጠይቀዋል።
ቤታቸውን የሚያከራዩ ነዋሪዎች የተከራዮችን ማንነት ሊያጣሩ እና ተገቢውን መረጃ ሊይዙ ይገባልም ብለዋል።