የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ እንደገለፁት በከተማ አስተዳደሩ እስካሁን የነበሩ ተግባራትን ቆም ብሎ በማየት ሀገራዊ ለዉጡን ለማስቀጠል በመሬት፣ በቀበሌ ቤቶች፣ በጋራ መኖሪያ ቤቶች እና በህንፃዎች ላይ የኦዲት ሥራ እየተሰራ ነዉ፡፡
ምክትል ከንቲባዋ ˝የአዲስ ተስፋ ቀመር˝ በሚል መሪ ቃል አዲሱን ዓመት ለማክበር ጥላቻን በመቀነስ (-)፣ ያለንን በማካፈል (÷)፣ ይቅርታን በማባዛት (x)፣ በፍቅር በመደመር (+) በተጨባጭ በተግባር በመቀየር ሀገራዊ ለዉጡን እናስቀጥላለን ብለዋል፡፡
የመንግስት ኮሚኒዩኬሽን ጉዳዮች በድረ ገጹ እንደገለጸዉ መንግስት ለጀመረዉ የኦዲት ሥራ የከተማዋ ነዋሪዎች መረጃዎችን በመስጠት የበኩላቸዉን ድርሻ እንዲወጡም ጥሪ አቅርበዋል፡፡