በክብረ በዓሉ የመንግስተ አመራሮች፣ የኪነጥበብ ባለሞያዎች እንዲሁም በርካታ ቁጥር ያላቸአው ታዳሚዎች ተገኘተውበታል፡
የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስቴር ወ/ሮ ሶፊያ አሚን የህዝቦች አንድነት፣መፈቃቀር፣አብሮ የመኖር ትስስርን ከሚያጠናክሩ ጠቃሚ እሴቶች እና ክብረ በአላት መሃከል አሸንዳ አንዱ እንደሆነ ገልፀው እነዚህ እሴቶች የሰላም እና አንድነት ማገር ሆነው ከትውልድ ትውልድ ይተላለፉ ዘንድ ጠንክረን መስራት አለብን ብለዋል፡፡
የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ደ/ር አዲስ አለም ባሌማ በበኩላቸው የአሸንዳ በአል ከሃይማኖታዊ እና ባህላዊ አንድምታው ባሻገር የህዝብ ለህዝብ ትስስርን የሚፈጥር በመሆኑ በባህላዊ ቅርስነት በዩኔስኮ ለማስመዝገብ ከፍተኛ ጥረት ላይ መሆናቸውን በመክፈቻ ንግግራቸው ገልፀዋል፡፡