Uncategorized

የአሜሪካ መንግስት ልኡካን በኢትዮጵያ ጉብኝት ለማድረግ በዛሬው እለት አዲስ አበባ ይገባሉ።

በሪፐብሊካን ኮንግረስማን ክሪስቶፈር ስሚዝ የሚመራው የልኡካን ቡድን በኢትዮጵያ እየመጡ ባሉ ለውጦች ዙሪያ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አበይ አህመድ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር ተገናኝተው እንደሚወያይም ይጠበቃል።

የልኡኩ መሪ ኮንግረስማን ክርስቶፈር ስሚዝ ከአሜሪካ ድምፅ (ቪኦኤ) ራዲዮ ጋር ባደረጉት ቆይታ፥ በኢትዮጵያ በሚኖራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶክተር ወረቅነህ ጋር እንደሚወያዩ ገልፀዋል።

በውይይታቸውም በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የተጀመሩ ለውጦች ተጠናከረው በሚቀጥሉባቸው ጉዳዮች ላይ ምከክር እንደሚያደርጉ ነው ኮንግረስማኑ ያስታወቁት።

ልኡካኑ በኢትዮጵያ በሚኖረው ቆይታ ከሀይማኖት ተቋማት እና ከሲቪክ ማህበራት መሪዎች እንዲሁም ከጋዜጠኞች ጋር ተገናኝቶ በሰብአዊ መብት እና በዴሞክራሲ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሏል።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami