ያን ግዜ በተከሰተው የፀጥታ ችግር ህይወታቸውን ላጡና ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ለድጋፍ አጽድቋል፡፡
የቤንሻንጉል ጉምዝ ክልል መንግስት በግጭቱ ምክንያት ህይወታቸው ላለፈ 16 ግለሰቦች ቤተሰብ ለእያንዳንዳቸው 30 ሺ ብር፣ በግጭቱ ምክንያት ከባድ የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው 11 ግለሰቦች ለእያንዳንዳቸው 20ሺ ብር እንዲሁም በግጭቱ ምክንያት ቀላል ጉዳት ለደረሰባቸው 78 ግለሰቦች ደግሞ ለእያንዳንዳቸው 10 ሺ ብር ድጋፍ ለማድረግ ወስኗል፡፡
ከዚህ በተጨማሪ ክልሉ ንብረታቸው ለወደመባቸው ከ1ሺህ -5ሺ ብር ግምት ላለው ንብረት የቀረበው መጠን እንዲከፈል የወሰነ ሲሆን፣ ከብር 5001 ጀምሮ ያለውን ግምት በተመለከተ በ70% ተሰልቶ በድምሩ 589,665.40 ብር እንዲከፈላቸው መወሰኑንም ከኢቢሲ ያገኘዉን መረጃ ያመለክታል፡፡