ሲጂቲኤን እንደዘገበው ሁለቱ ሀገሮች ብድር እየተመላለሱ አንዱ በሌላው ላይ የታሪፍ ጭማሪ መቀጠሉን ተያይዘውታል፡፡
አሁን አሜሪካ በቻይና ምርቶች ላይ የ25 በመቶ የታሪፍ ጭማሪ መጣሏን ተከትሎ ቻይናም በብርሃን ፍጥነት በዋሽንግተን ምርቶች ላይ ተመሳሳይ ታሪፍ ጥላባቸዋለች፡፡
አሜሪካ የ25 በመቶ ታሪፍ የጣለችው ከቻይና ወደ ሀገሯ በሚገቡ የኤሌክትሮኒክስ፣ የፕላስቲክ፣ የባቡር መገጣጠሚያ መሳሪያዎችና የኬሚካል ውጤቶች ላይ ሲሆን ቻይና በአጸፋው በተሸከርካሪዎች፣ በኢነርጂና በኬሚካል ጥሬ እቃዎች ላይ ተመሳሳይ ታሪፍ ጥላለች፡፡