ይህንን ያለዉ የአዲስ አበባ ዉሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ነዉ፡፡
በባለስልጣኑ የኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች የስራ ሄደት መሪ አቶ እስጢፋኖስ ብስራት ለአርትስ ቲቪ በትላንትናው ዕለት አቃቂ አካባቢ የደረሰውን የጎርፍ አደጋ ተከትሎ በተለያዩ ማህበራዊ ድረገፆች ላይ የአቃቂ ግድብ ሞልቶ ለማስተንፈስ በተደረገ ጥረት ውስጥ ቸግሩ እንደተከሰተ እና የሚመለከተውም አካል ማስጠንቀቄያ እንዳልተሰጠ ተደርጎ ሲነገር የነበረዉ ሀሰት ነዉ ብለዋል፡፡፡
በክረምት ሁሌ የማስተንፈስ ስራ እንደሚሰራም ተናግረዋል፡፡ በትላንትናውም ዕለት የደረሰውም አደጋ ከባድ ዝናብ ከመዝነቡ ጋር ተያይዞ እና ሌሎች ገባር ወንዞች ተቀላቅለው ሜዳው ላይ ውሃው በመተኛቱ እየተፈጠረ አደጋ እንደነበር አስታዉሰዋል፡፡
አቶ አስጢፋኖስ የሚለቀቀው ውሃ በአካባቢው ያሉ ነዋሪዎች ላይ አደጋ እንዳያስከተልና ህብረተስቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ በመገናኛ ብዙሃን ከሃምሌ 1 ቀን ጀምሮ ማስታወቂያ ሲነገር እንደቆየም ለጣቢያችን ገልጸዋል፡፡
አሁንም የማስጠንቀቅያዉ መልእክት በተለይ ለአደጋዉ ተጋላጭ ለሆኑ የአካባቢዉ ነዋሪዎች እንዲደርስ እየተደረገ ነዉ ብለዋል፡፡