EthiopiaPolitics

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ብአዴን ወደፊት የሚመራባቸውን የፖለቲካ መስመሮች ለመወሰን እየመከረ ነው፡፡ 

የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ ይመራበት የነበረውን አብዮታዊ ዲሞክራሲ እናሻሽል ወይም አናሻሸል በሚሉ እና ሌሎች መሰረታዊ ጉዳዮች ላይ እየመከረ ነው፡፡
በዋናነትም አብዮታዊ ዴሞክራሲን እናሻሽል ወይም አናሻሸል? በሚል መሰረታዊ የማሻሻያ ጉዳዮችይወያያል፡፡ የድርጅቱ ስያሜ እና ዓርማ የአማራን ህዝብ አይወክልም በመባሉም ይመከርበታል፡፡ ድርጅቱ ባለፉት ጊዜያት ይመራባቸው የነበሩ ህጎች አንዳንዶቹ ወቅቱን ያላገናዘቡ በመሆኑ ይመከርባቸዋል፡
የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ በክልሉ ካሉ አመራሮች የሰበሰባቸውን መሰረታዊ የማሻሻያ ጉዳዮች ላይ ለመነጋገር እና ድርጅቱ በቀጣይ ስለሚከተላቸው የፖለቲካ መስመሮች ላይ ለመወሰን እየመከረ ነው፡፡
የብአዴን ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል እና በብአዴን ጽ/ቤት የገጠር ፖለቲካ ና አደረጃጀት ዘርፍ ኃላፊ አቶ ምግባሩ ከበደ ማዕከላዊ ኮሚቴው በ12ኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ የሚቀርቡ አጀንዳዎችን በተመለከተ ከፍተኛ ጊዜ ሰጥቶ ይወያያል ብለዋል፡፡
ብአዴን ከ11ኛ መደበኛ ጉባኤ በኋላ ባሉት ሶስት ዓመታት የታዩ ለውጦችን ይገመግማል፡፡
ማዕከላዊ ኮሚቴው በ12ኛው መደበኛ ጉባኤ ላይ ድርጅቱ ሊያሻሽላቸው የሚገቡ ጉዳዮችን ለይቶ ለማቅረብ እንዲቻል ትኩረት ሰጥቶ እንደሚወያይ የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ዘግቧል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami