አርትስ 18/12/2010
የአሜሪካ ኮንግረንስ አባላት ልኡካን ቡድን ከኢፌዲሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ጋር በአዲስ አበባ ተወያይቷል፡፡
የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረ ገጹ እንዳስታወቀዉ ኮንግረንስማን ክሪስ ስሚዝ አሁን እየተካሄደ ያለው ለውጥ ተጠናክሮ እንዲቀጠል ጥሪ አቅርበዋል፡፡
የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ አሜሪካ ለኢትዮጵያ ዕድገት ለምታደርገው አስተዋጽኦ አድናቆታቸውን ገልጸዋል፡፡
የአሜሪካ ኮንግረስ አስፈላጊውን ድጋፍ እንዲያደርግ ጠይቀው እስከ አሁን ለተደረገው ድጋፍም ምስጋና አቅርበዋል፡፡
አገራችን በልማት፣ በዴሞክራሲ፣ በመልካም አስተዳደር እና በሰብአዊ መብት አያያዝ ዙሪያ ከአሜሪካ ጋር መስራቷን እንደምትቀጠል ተናግረዋል፡፡
ኢትዮጵያ አሸባሪነትን በመዋጋት እና በቀጠናው ሰላም እንዲሰፍን በማድረግ እረገድ የአሜሪካ ጠንካራ አጋር መሆኗን ፤ይህም ወደፊት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አገራችን በጋራ ትሰራለች በማለት ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ተናግረዋል፡፡