የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ልዩ ሀላፊ አቶ ፍፁም አረጋ በቲዉተር ገፃቸው አንዳስታውቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ፕሬዝዳንት ትራን ዳይኩአንግን በፅህፈት ቤታቸዉ ተቀብለዉ አነጋግረዋቸዋል፡፡
መሪዎቹ በሁለቱ ሀገራት ባህል፣ ኢኮኖሚ፣ ሳይንስና ቴክኖሎጂ አጀንዳዎች ዙሪያ ተወያይተዋል፡፡ በተጨማሪም በኢንቨስትመንት እና በቪዛ አገልግሎት ሁለቱ ሀገራት ተባብረው መስራት የሚያስችላቸውን የጋራ መግባቢያ ስምምነቶችን ተፈራርመዋል፡፡
የቬትናሙ ግሬዝደንት በኢትዮጵያ የሶስት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ በትላንትነው ዕለት አዲስ አበባ መግባታቸዉ ይታወሳል፡፡