ከመንግስት ኮምንኬሽን ጉዳች ደረ-ገፅ ያገኘነው መረጃ እንደሚያመለክተው በአዲስ አበባ ዩንቨርስቲ የፖለቲካል ሳይንስና አለም አቀፍ ግንኙነት መምህሩ ዶክተር መረራ ጉዲና የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን የቦርድ አባል በመሆን እያገለገለሉ ይገኛሉ።
ዶክተር መረራ ወደ ሀላፊነት ከመጡ ጀምሮ በተቋሙ ስብሰባዎች ላይ እየተሳተፉ እንደሆነ ገልጸዋል።
በተቋሙ ያለው የቴክኖሎጂ አጠቃቀም የሚያሰራ ነው ያሉት ዶክተር መረራ እስካሁን ከቦርድ አመራር አባላት ጋር በነበራቸው ውይይት የበጀት የአሰራርና ሌሎች ጉዳዮችን አንስተው መነጋገራቸውን አስታውቀዋል።
ኢቢሲ የብዝሀነትና የህዳሴ ድምፅ የሚለውን መፈክሩን አጠናክሮ እንዲቀጥልና የህዝብ ድምፅ መሆኑን እንዲያረጋግጥ የበኩሌን እወጣለውም ብለዋል።