የቀድሞዋ የደቡብ ኮሪያ ፕሬዝንት ፓርክ ጉን ሄይ በ2017 በሙስና ወንጀል ተከሰው ጥፋተኛ በመባላቸው የ24 ዓመት አስራት ተፈርዶባቸው ነበር፡፡
በአልጀዚራ እንደዘገበው ፕሬዝዳንቷ የእስር ጊዜያቸው እንዲቀንስላቸው አቤት ቢሉም ይግባኝ ሰሚ ፍርድ ቤቱ ውሳኔው አንድ ዓመት አሳድጎ በ25 ዓመት እንዲቀጡ ወስኖባቸዋል፡፡
ፍርድ ቤቱ ፕሬዝዳንት ፓርክ ከእስር በተጨማሪ ተጥሎባቸው የነበረው የገንዘብ ቅጣትም ከፍ እንዲል ወስኗል፡፡
በዚህም መሰረት በታችኛው ፍርድ ቤት ተወስኖባቸው የነበረው የ16 ሚሊዮን ዶላር ቅጣት ወደ 17.8 ሚሊዮን ዶላር ከፍ ብሏል፡፡