የዚምባቡየው ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋ አወዛጋቢውን የምርጫ ውጤት በአሸናፊነት አጠቃለውታል፡፡
አናዶሉ የዜና ወኪል እንደዘገበው ምናንጋግዋ ከ37 ዓመት ወዲህ የሀገሪቱ የመጀመሪያው በምርጫ ወደ ስልጣን የመጡ መሪ በመሆን አዲስ ታሪክ አስመዝግበዋል፡፡
ምርጨውን አጭበርብረዋል ተብለው በተፎካካሪያቸው ወቀሳ የደረሰባቸው ፕሬዝዳንቱ አሁን በጋራ ሀገራችንን የምናሳድግበት ወቅት ስለሆነ አንድነታችንን እናጠናክር የሚል መልእክት አስተላልፈዋል፡፡
ምናንጋግዋ በሚቀጥሉት 11 ዓመታት ውስጥ ከድህነት የተላቀቀች፣ ህዘወቦቿ መካከለኛ ገቢ ያላቸውና ከሙስና የጸዳች ዚምባቡየን ለመፍጠር ተግተን እንሰራለን ብለዋል፡፡
የቀድሞው ፕሬዝዳንት ሮበርት ሙጋቤን ጨምሮ በርካታ የሀገር መሪዎችም የአእንኳን ደስ ያለዎት መልእክት ልከውላቸዋል፡፡