Uncategorized

በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተቀበረ ቦምብ አሁንም ሰዎችን እያፈናቀለ ነው፡፡

በማእከላዊ ጀርመን ሉድዊግሽፈን በተባለች ከተማ ከ18 ሽህ በላይ ነዋሪዎች በፍጥነት አካባቢያቸወን ለቀው እንዲወጡ ተደርጓል፡፡

ምክንያቱ ደግሞ በሁለተኛው የዓለም ጦርነት የተቀበረ ቦምብ እስካሁን ሳይፈነዳ በመገኘቱ አደጋ እንዳይደርስባቸው ታስቦ ነው፡፡

ቢቢሲ እንደዘገበው የግንባታ ሰራተኞች በቁፋሮ ላያ ሳሉ ያገኙት ይህ ቦምብ 500 ኪሎ ግራም ክብደት አለው፡፡

ባለሞያዎች ቦምቡ በወቅቱ በናዚ ወታደሮች ላይ የዘመቱ የአሜሪካ ተዋጊ ሀይሎች የተጠቀሙበት እነደሆነ ጥርጣሬ አላቸው፡፡

በጀርመን ፍራንክፈርት ከተማ በፈረንጆቹ 2017 በተመሳሳይ ችግር ከ70 ሽህ በላይ ሰዎች    አካባቢያቸውን ለቀው እንዲወጡ መደረጉ ይታወሳል፡፡

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami