ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ እንዳሉት ድጋፉ በቀጥታ የሀገሪቱን በጀት የሚደግፍ ነው፡፡
አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የዓለም ባንክን ጨምሮ ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት በ97 በኢትዮጵያ በተካሄደው ምርጫ የተከሰተውን ቀውስ ተከትሎ ለቀጥታ በጀት የሚውል የገንዘብ ድጋፍ አድርገው አያውቁም፡፡
ለገንዘቡ መገኘት አሁን በኢትዮጵያ የመጣው ለውጥ ዋኛው ምክንያት መሆኑንም ዶክተር አብይ ተናግረዋል፡፡
የዓለም ባንክ ግሩፕ ፕሬዝዳንት ጂም ያንግ ኪም በበኩላቸው አሁን ላይ በኢትዮጵያ እየታየ ያለውን መልካም የለውጥ ጅምር ለመደገፍ ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡