የእንግሊዟ ጠቅላይ ሚንስትር ቴሬዛ ሜይ የመጀመሪያ የአፍሪካ ጉብኝታቸውን ጀምረዋል፡፡
ቢቢሲ እንደዘገበው ጠቅላይ ሚንስትሯ ጉብኝታቸውን የጀመሩት በደቡብ አፍሪካ ነው፡፡ ቀጥሎ ናይጀሪያና ኬንያን የመጎብኘት ፕሮገራምም ተይዞላቸዋል፡፡
ሜይ የአፍሪካ ጉዟቸው ዋነኛ ዓላማ ሀገራቸው ከአውሮፓ ህብረት በይፋ ከተፋታች በኋላ በአፍሪካ አህጉር በንግድና በኢንቨስትመንት ንቁ ተሳትፎ ለማድረግ ማሰቧን ለማብሰር ነው፡፡
ጠቅላይ ሚንስትሯ በአፍሪካ ቆይታቸው የደቡብ አፍሪካ፣ የናይጀሪያና የኬንያ ፕሬዝዳንቶች ጋር ተገናኝተው በእንግሊዝ እና በአፍሪካ መካከል ያለውን የንግድና የኢንቨስትመንት ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ይወያያሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
እንግሊዝ በ2019 ከአውሮፓ ህብረት ጋር በይፋ መለያየቷን ካረጋገጠች በኋላ ፊቷን ወደ አፍሪካ ለማዞርና በአህጉሪቱ ኢንቨስት በማድረግ ከቡድን 7 አባል ሀገራት ቀዳሚ የመሆን እቅድ እንዳላትም ዘገባው አመላክቷል፡፡ ይሄ ውጥንም እስከ 2022 ተግባራዊ ይሆናል ነው የተባለው፡፡