EconomyEthiopiaSocial

17 ሺህ 700 የ40/60 ቤቶችን እስከ መጪው ጥቅምት 30 ቀን ድረስ ለተጠቃሚዎች ሊተላለፉ ነው፡፡

17 ሺህ 700 የ40/60 ቤቶችን እስከ መጪው ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ እንደሚገኝ የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርኘራይዝ አስታወቀ፡፡
የአዲስ አበባ ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ በድረ ገፁ እንዳስነበበው በተያዘው በጀት ዓመት 8 ሺህ ቤቶችን ግንባታ ለማካሄድ የበጀት እና የመሬት ዝግጅት መጠናቀቁን ገልጽዋል፡፡
የአዲስ አበባ ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርኘራይዝ በግንባታ ላይ ያሉትን የ40/60 ቤቶች በፍጥነት አጠናቆ ለህብረተሰቡ ለማስተላላፍ እና በ2011 አዳዲስ ቤቶች ግንባታ ለማካሄድ የቅድመ ዝግጅት ስራን በተመለከተ በየደረጃው ከሚገኙ አመራሮች እና ሰራተኞች ጋር ውይይት አካሂዷል፡፡
በውይይቱ ላይ የኢንተርኘራይዙ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኮንን አምባዬ እንዳስታወቁት በሰባት ሳይቶች ግንባታቸው የተገባደዱ የ40/60 ቤቶች ቁጥራቸው 17 ሺህ 700 ቤቶችን እስከ ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም ድረስ ለተጠቃሚዎች ለማስተላለፍ የማጠቃለያ ስራዎች እየተሰራ ይገኛል ብለዋል፡፡
ለተጠቃሚዎች ከሚተላለፉት 17 ሺህ 700 ቤቶች ውስጥ 4 ሺህ ያህሉ የንግድ ቤቶች ሲሆኑ እነዚህን ቤቶች በግልጽ ጨረታ በመሸጥ ለቤቶች ግንባታ መደጎሚያ እንደሚውሉ ተናግረዋል፡፡
በተጨማሪም በተያዘው በጀት ዓመት ከ8 ሺህ በላይ ቤቶችን ለመገንባት ከበጀት ምደባ ጀምሮ የመሬት ዝግጅት መጠናቀቁ የገለጹት ዋና ዳይሬክተሩ ለግንባታው የሚሰማሩ አማካሪ ድርጅቶች መረጣ በመካሄድ ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡
ኢንተርኘራይዙ ከ38 ሺህ በላይ ቤቶችን በአስራ አንድ ሳይቶች ግንባታ በማካሄድ ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami