EthiopiaPoliticsRegionsUncategorized

ኢህአዴግ በዛሬው የጉባዔው ውሎ የተደራጀ ሌብነት እና ዘረፋ የማይታለፉ ቀይ መስመሮቼ ናቸው አለ

አርትስ 24/01/2011
11ኛ ጉባኤውን እያካሄደ የሚገኘው ኢህአዴግ ዛሬ ባለፉት ጊዜያት በተከናወኑ አበይት ጉዳዮች ላይ መወያየቱን የገለፁት የጉባዔው ቃል አቀባይ አቶ ፍቃዱ ተሰማ ናቸው።
ቃል አቀባዩ እንደተናገሩት ድርጅቱ የአዲስ እመርታ ለውጥ መርሆችንም አስቀምጧል። ከዚህ ቀዳሚው ዕርቀ ሰላም ሲሆን ያለፈውን የጥፋት ዶሴ ዘግቶ ስለለውጥ ማሰብና የወደፊቱን ማየት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ መደመር ነው፤አብሮ ተዋዶ የአገርን ልዕልና ማስጠበቅ።
በተጨማሪም ድርጅቱ የማይታለፍ ቀይ መስመር በማለት የተደራጀ ሌብነትና ዘረፋ እንዲሁም ሥርዓት አልበኝነትን አልታገስም ብሏል።
ህግና ስርዓት መከበር አለበት ሲልም አቋሙን አስቀምጧል።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami