EthiopiaRegionsSocial

የእንቦጭ አረምን ለማጥፋት በጣና ትረስት ፈንድ የተሰበሰበው 32 ነጥብ 8 ሚሊየን ብር ወደ ስራ ሊገባ ነው

አርትስ 23/02/2011

በጣና ሀይቅ የተከሰተውን እንቦጭ አረም አወጋገድ የ2010 አፈፃፀምና ግምገማ እንዲሁም የ2011 ዕቅድን በተመለከተ  በዛሬው ዕለት  የአማራ ክልልመንግስት ውይይት አካሂዷል።

በዚህ ወቅት በጣና ትረስት ፈንድ የተሰበሰበው ገንዘብ  ጠፍቷል ተብሎ የሚሰራጨው ወሬ የተሳሳተ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፥ ገንዘቡ በቀጣይ ሳምንት ወደ ስራእንደሚገባ ተጠቁሟል።

በመድረኩ የ2010 ዓመተ ምህረት የህብረተሰብ ተሳትፎ ከፍተኛ እንደነበረና የእንቦጭ አረም መቀነሱ የተገለፀ ሲሆን፤ በዚህም በ2009/10 ከፍተኛ የነበረውየአንቦጭ አረም በአሁን ወቅት ቀንሷል ተብሏል።

በ2011 ዓመተ ምህረት  የእንቦጭ አረምን ለመቀነስ በተጠና መንገድ መሰራት እንዳለበት ድምዳሜ ላይ ተደርሷል።

የእንቦጭ አረምን በቀጣይ አርሶ አደሩን፣ ወጣቶች እና ዘመናዊ ማሽኖችን በመጠቀም የመከላከል ስራ እንደሚከናወን ርዕሰ መስተዳድር ገዱ አንዳጋቸውአስታውቀዋል።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami