EthiopiaPoliticsRegionsSocial

የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግስትን ለማደስ የሚያስችል ስምምነት ተፈረመ

አርትስ 23/02/2011

 

ስምምነቱን በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ተወካይ እና የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ደስታ ተፈራርመዋል።

የአሜሪካ ኤምባሲ ለአርትስ በላከዉ በግለጫ እንዳስታወቀዉ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክል ራይነር በትናንትናው ዕለት ከፌደራል እና ክልልመንግስታት አመራሮች ጋር በመሆን የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግስትን ጎብኝተዋል።

በዛሬው ዕለትም የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግስትን ለማደስ እና ለመጠገን የሚያስችል ስምምነት የጅማ ከተማ አመራሮች እና የከተማዋ ነዋሪዎችበተገኙበት ተፈርሟል።

የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግስትን ለመጠገን እና ለማደስም የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን፣ የኦሮሚያ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ እና የአሜሪካ ኤምባሲ 7 ነጥብ9 ሚሊየን ብር መድበው በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ።

አሜሪካ ከዚህ ቀደም የጅማ አባ ጅፋር ቤተ መንግስትን ለመጠገን እና ለማደስ ድጋፍ እንደምታደርግ መግለጿ ይታወሳል።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami