አርትስ 23/02/2011
ህብረቱ ከሁሉም ክልሎች እና 2 ከተማ አስተዳደሮች የተውጣጡ አባላትን ያቀፈ ሲሆን፥ በአዳማ ከተማ በዛሬው እለት መመስረቱ ነው የተገለጸው።
ህብረቱ በትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ የሚመራ ሆኖ እያንዳንዱን ክልል የሚወክሉ 11 የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴዎች እንዳሉትም ተነግሯል።
በህብረቱ ምስረታም ኢንጂነር ጌታቸው ስመኝን ከአዲስ አበባ ሊቀመምበር ፣ ወ/ሮ መሰረት ተክሌ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ምክትል ሊቀመምበር እና አቶሁሴን በዳሶን ከኦሮሚያ ክልል ጸሃፊ ሆነው ተመርጠዋል።
የህብረቱ ዋና ዓላማ የተማሪ ወላጆች በተዋረድ ከመንግስት ጋር የሚገናኙበት መዋቅር በመዘርጋት የትምህርት ጥራት መረጋገጥ ላይ በጋራ ለመስራት ሲሆን፥ምክር ቤት እንደሚኖረውም ነው የተገለጸው።