አርትስ 23/02/2011
የዚምባቡዌ ፕሬዚዳንት ኤመርሰን ምናጋግዋ በሀገሪቱ ሰሜናዊ ክፍል በምትገኘው ሙዛራባኒ ከተማ ነዳጅ እና የጋዝ ክምችት መገኘቱን ተናግረዋል፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበዉ የአውስትራሊያ ኩባንያ በሆነው ኢንቪክትስ ኢነርጂ አማካኝነት የተገኘው ይህ ነዳጅ እና የጋዝ ክምችት በአገሪቱ ታሪክ የመጀመሪያ ነዉ ተብሏል፡፡
ፕሬዝዳንቱ ኩባንያውን በመጪው የፈረንጆቹ አመት በ2020 አጋማሽ ላይ ስራ ለማስጀመር በቅርብ እየሰሩ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የማዕድን ሚኒስትሩ ዊንስተን ቺታንዶ ስራውን ለማከናወን ወደ 20 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ወጪ ይደረጋል ብለዋል፡፡
በፈረንጆቹ በ1990 ሞቢል በሙዛራባኒ የነዳጅ እና የጋዝ ክምችት ፍለጋ ጀምሮ የነበረ ቢሆንም፤ በመሃል ስራውን በማቋረጡ ኢንቪክትስ ኢነርጂ ስራውንተረክቦ የፍለጋ ስራ ሲያከናውን መቆየቱ ተነግሯል፡፡