በዘንድሮው የብሔር ብሔረሰቦችና ህዝቦች ቀን 10 ሺህ ሰዎችን ቡና የማጠጣት ስነ ስርዓት ይከናወናል
አርትስ 26/02/2011
በ13ኛው የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች በዓል ኢትዮጵያን በአለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ ለማስፈር ነው 10 ሺህ ሰዎች በሚሳተፉበት የቡና መጠጣት ስነስርዓት እንደሚከናወን የአዲስ አበባ ከተማአስተዳደር ያስታወቀው
በአዲስ አበባ ከተማ የሚከበረውን የብሄር ብሄረሰቦች በዓልን አስመልክቶ ውይይት ተካሄዷል።
” አብረን ቡና እንጠጣ” በሚል መሪ ቃል በአለም የድንቃ ድንቅ መዝገብ የሚሰፍር ታላቅ የቡና መጠጣት ስነስርዓት እንደሚካሄድ የተገለፀ ሲሆን፥ በ5 ሰዓታት ከ10 ሺህ ሰዎች በላይ ሰዎች ይሳተፉበታልተብሏል።
የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦች በአል ኢትዮጵያዊነትን በሚያጎላ መንገድ ለማክበር መዘጋጀቱን አስተዳደሩ አስታውቋል፡፡
በበአሉ ላይ ከየክልሉ ከ1 ሺህ 200 እስከ 1 ሺህ 500 የሚደርሱ እንግዶች ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ሲሆን፥ መዲናዋ እንግዶቿን ለመቀበል እየተዘጋጀች መሆኗን አዘጋጆቹ ገልፀዋል፡፡ በበዓሉ ላይ የተለያዩ ስነስርዓቶችም ይከናወናሉ፡፡