EconomyEthiopiaHealthSocial

የምሥራቅ እና የደቡብ አፍሪካ ሀገራት የወባ መቆጣጠር አህጉራዊ ጉባዔ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ነው

አርትስ 28/02/2011

የሮል ባክ ማላሪያ ፓርትነርሺኘ ቱ ኢንድ ማላሪያ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዶክተር ከሰተብርሃን አድማሱ በጉብዔው መክፈቻ እንደተናገሩት በአለም አቀፍ ደረጃ ወባን ለማጥፋት የተቀመጠውን ግብ ለማሳካት ከፍተኛ የወባጫና ባለባቸው ሀገራት የወባ ክስተትን ዜሮ ለማድረግ ያለመ ኘሮግራም ይፋ መደረጉን ተናግረው ፤ወባን ለማጥፋት ያለው አጋርነት በዘርፉ የሚሰሩ አካላት ቅንጅታዊ አሠራር መጐልበትና ድንበር ተሻጋሪ ትብብሮችንእውን ማድረግ አስፈላጊ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ለ5 ቀናት በሚቆየው ጉባዔም ሀገሪቱ ወባን በማጥፋት ዙሪያ ምርጥ ልምዶችን፣ እውቀቶችን፣ ተሞክሮዎችን፣ መረጃዎችን ተግዳሮቶችን እና ማነቆዎችን የሚለዋውጡበት መልካም አጋጣሚ ለመፍጠር እንደሆነገልፀዋል፡፡
የጤና ጥበቃ ሚኒስትር ዶከተር አሚር አማን ባደረጉት የመክፈቻ ንግግርም ባለፉት ቅርብ አመታት የወባ በሽታ በኢትዮጵያ በግንባር ቀደምነት ከሚጠቀሱ የማህበረሰብ የጤና ችግሮች መካከል አንዱ እንደነበርአስታውሰው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ወባን ለማጥፋት የሚያግዙ እርምጃዎችን ተግባራዊ በማድረጉ እና በተዘረጋው የጤና ኤክስቴንሽን መርሃግብር የጤና አገልግሎት አቅርቦትን በማሻሻሉ በወባ ምክንያት የሚከሰትበሽታንና ሞትን መቆጣጠር መቻሉን ተናግረዋል፡፡

የጤና ጥበቃ እንደገለፀው ዓለም አቀፍ ተቋማት የተለያዩ የተሳተፉ አመራሮቸ በሰጡት አስተያየትም ኢትዮጵያ ወባን በማጥፋት ዙሪያ ያከናወነቻቸው ተግባራት ሌሎች ሀገሮችም ልምድ ሊወስዱበት የሚገባ እንደሆነተናግረዋል፡፡

 

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami