EthiopiaSport

የኢትዮጵያ አገር አቋራጭ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በመጭው እሁድ ይከናወናል

አርትስ ስፖርት 28/2011

ውድድሩ በሱሉልታ ከተማ፣ ከታ ወሌሌ – ወሌሉቤ ቀበሌ በመጭው እሁድ ህዳር 2/2011 ዓ. ም. ከማለዳው 1፡00 ሰዓት ጀምሮ እንደሚያካሂድ ዛሬ የኢትዮጵያ አትሌቲክፌዴሬሽን ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል፡፡ የፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ቢልልኝ መቆያ እንደገለጹት የውድድሩ አላማ ክልሎች፣ ከተማ አስተዳደሮች፣ ክለቦችና ተቋማትን በሃገር አቀፍየአገር አቋራጭ ውድድር ላይ በማሳተፍ ለተተኪ አትሌቶች እድል መፍጠር ነው፡፡ በዚህ አገር አቋራጭ ውድድር ላይ 92 ሴት፣ 177 ወንድ፣ በአጠቃላይ 269 አትሌቶች የሚካፈሉሲሆን የግልና አንጋፋ አትሌቶችን ጨምሮ 18 ቡድኖች መመዝገባቸውም ተገልጧል፡፡ የፌዴሬሽኑ የቴክኒክ ኃላፊ አቶ ዱቤ ጅሎ፡ የውድድሮቹ ካታጎሪዎች በአዋቂ ምድብ ወንዶች12 ኪ. ሜ፣ ሴቶች 8 ኪ.ሜ.፣ በድብልቅ ሪሌይ ሁለቱም ጾታ በ8 ኪ. ሜ፣ 8 ኪ. ሜ አትሌቶች እንደሚካፈሉበት አስረድተዋል፡፡ በውድድሩ ከሚሳተፉ አትሌቶች መካከል፡በወንዶች አትሌት ታዬ ግርማ፣ ተስፋዬ ድሪባ፣ ገብሬ እርቅ ይሁን፣ ያሲን ሃጂ እና ሃይማኖት አለው፤ እንዲሁም በሴቶች አትሌት ፋንቱ ወርቁ፣ ሃዊ አለሙ፣ አለሚቱ ሃዊ፣ ገበያነሽ አየለሃዊፈይሳ እና ብርቱካን አዳሙ ተጠቅሰዋል፡፡ ፌዴሬሽኑ በሁሉም የውድድር ፈርጆች ከወርቅ እስከ ነሃስ የሜዳልያ ሽልማት እና የማበረታቻ ገንዘብ ሽልማት ይሰጣል፡፡ ለውድድሩምበአጠቃላይ 150,000 ብር ለሽልማት እንዳዘጋጀ ተገልጧል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami