የዴቪድ ቤካም ቡድን ስታዲየም ግንባታ አልጋ ባልጋ ሆኖለታል
አርትስ ስፖርት 29/02/2011
የቀድሞ ዝነኛ እግር ኳስ ተጫዋች ዴቪድ ቤካም ንብረት የሆነው ኢንተር ሚያሚ እግር ኳስ ክለብ፤ አዲስ ስታዲየም ለመገንባት ባቀረበው ጥያቄ መሰረት የአካባቢው ማህበረሰብ በሰጡት ድምፅይሁንታን ማግኘቱን ተከትሎ ነው ለሜጀር ሊግ ሶከር ውድድር ለመካፈል በሚያደርገው ጉዞ መንገዱን እያሰማመረ የሚገኘው፡፡ የስታዲየም ግንባታው ቤቶች፣ ሱቆች፣ ሆቴሎችንና የህዝብ የመኪናማቆሚያዎችን ያጠቃልላል ተብሏል፡፡ የቤካም አጋሮች ከከተማዋ አምስት ኮሚሽነሮች የአራቱን ድጋፍ ማግኘት ችለዋልም ተብሏል፡፡ የቀድሞ የእንግሊዝ ብሄራዊ ቡድን አምበል ዴቪድ ቤካም እኛንወግናችሁ ለቆማችሁ ደጋፊዎች በሞላ ምስጋናየ ይደረሳችሁ ብሏል፡፡ አክሎም ‹‹ዛሬ አስደሳች ቀን ነው፤ ምክንያቱም ለዚህ ታላቅ ከተማ ህልም የነበረውን እግር ኳስ ቡድን መሰረት ጥለናልና፤ ነገር ግንአሁንም ማሸነፍ አለብን፤ እኔም እዚህ የመጣሁት ማራኪ ቡድን ብቻ ለማቋቋም ብቻ አይደለም፤ ቻምፒዮንሽፖችን ማሸነፍ ለእኔ አስፈላጊው ነገር ነው›› ብሏል፡፡ ባሳለፍነው የፈረንጆች ጥር ወር ኢንተርሚያሚ እ.አ.አ በ2020 የሜጀር ሊግ ሶከር እንዲሳተፍ ፍቃድ አግኝቷል፡፡ ቢቢሲ