EthiopiaNews

ኢትዮጵያ የባህር ሃይሏን በቀይ ባህር እና በህንድ ውቅያኖስ አቅራቢያ ለመገንባት ወስናለች

ኢትዮጵያ የባህር ሃይሏን በቀይ ባህር እና በህንድ ውቅያኖስ አቅራቢያ ለመገንባት ወስናለች

አርትስ 29/02/2011

 ኢትዮጵያ የባህር ሃይል እንዲኖራት መንግስት ትኩረት ሰጥቶ እየሰራበት መሆኑን የገለጹት የጦር ሃይሎች ምክትል ኤታማዦር ሹም ጀኔራል ብረሃኑ ጁላ የባህር ሃይል ቤዙም በቀይ ባህር እና በህንድ ውቂያኖስ አቅራቢያ እንዲገነባ ውሳኔ መተላለፉን ተናግረዋል።

ውሳኔው የተላለፈው ጠቅላይ ሚኒስቴር ዶክተር አብይ አህመድ በሃገሪቱ በቴክኖሎጂ የታገዘ ጠንካራ የባህር ሃይል ለመገንባት ታቅዷል ማለታቸውን ተከትሎ ነው።

በዚህ መሰረትም ኢትዮጲያ የራሷ ባህር ባይኖራትም ለቀይ ባህር እና ለህንድ ውቂያኖስ ያላትን ቅርበት በመጠቀም ከባህር ዳርቻው 60 ኪሎሜትር ርቀት ላይ የባህር ሃይሏን እንደምትገነባ ጀነራሉ ለኢትዮጲያ ፕሬስ ድርጅት ተናግረዋል፡፡

የባህር ሃይሉ  የውጭ አካላትን ለመቆጣጠር ስለሚኖረው  አቅም፣ ቁጥጥር እና መዋቅር ከሌሎች በዘርፉ ልምድ ካላቸው ሃገራት ጋር እየተማከርን ነው ያሉት ጀኔራሉ ኢትዮጵያ ቀይ ባህርን ከውጭሃገር ለሚገቡ እና ከሃገር ለሚወጡ የንግድ እቃዎች እንደምትጠቀም ሁሉ ጠንካራ የባህር ሃይል ለመገንባትም ትገለገልበታለች ብለዋል።

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami