ላይቤሪያዊቷ የኖቤል ተሸላሚ የ2018 የቦን ኢንተርናሽናል ተመራጭ ሆነዋል
አርትስ 12/03/2011
ሎሬት ሌይማህ ግቦዊ በፈረንጆቹ 2011 ከላይቤሪያዋ ፕሬዝዳንት ኤለን ጆንሰን ሰርሊፍና ከየመናዊዋ ታወኮል ካርማን ጋር በጋራ የሰላም ኖቤል ሽልማትን አሸንፈዋል፡፡
አሁን ደግሞ የ2018 የቦን ኢንተርናሽናል የዴሞክራሲ ሽልማት አሸናፊ በመሆን 10 ሺሀ ዩሮ ተበርክቶላቸዋል፡፡
አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የአሁኑ ሽልማት ለላይረቤሪያዊያን መብት አጥብቀው በመታገላቸውና በዓለም አቀፍ ደረጃ ለሴቶች ለሴቶች እኩልነት ባደረጉት ተጋድሎ ነው የተሰጣቸው፡፡
ቦን ኢንተርናሽናል የዴሞክራሲ ሽልማት በየ ሁለት ዓመቱ የሚከናወን ሲሆን ለሰው ልጆች መብት ተግተው የሚሰሩና ዴሞክራሲን ለሚያበረታቱ ግለሰቦችን ተቋማት ይሰጣል፡፡
ግቦዊ በሚኖሩበት ማህረበረሰብ ውስጥ ሰላም እና የኑሮ መሻሻል እንዲመጣ አጥብቀው በሚታገሉ ሴቶች ስም ነው ሽልመቱን የተቀበልኩት ብለዋል፡፡