ሪያድና ዋሽንግተን ግንኙነታቸው ነፋስ ገብቶበታል
አርትስ 12/03/2011
የሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሲ አይ ኤ በጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ግድያ ዙሪያ ያወጣውን ሪፖርት መሰረተ ቢስ ነው ብሎታል፡፡
ሮይተርስ እንደዘገበው የሳውዲ መንግስት ጋዜጠኛው እንዲገደል ልኡል አልጋ ወራሽ ሞሀመድ ቢን ሳልማን ትእዛዝ ሰጥተዋል የሚለውን የአሜሪካን መግለጫ በፅኑ ተቃውሞታል፡፡
የሳውዲ አረቢያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አብደል አል ጁቢር በአልጋ ወራሹ ላይ የሚነዛውን አሉባልታ አጥብቀን እንቃወማለን በማለት አልሻርቅ አል ዋስት ለተባለው ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡
ባለፈው ሳምንት የተለያዩ መገናኛ ብዙሀን ሲአይኤን ጠቅሰው ባሰራጩት ዘገባዎቻቸው የካሾጊ ገድያ ከሳውዲው ንጉስ ጋር የተገናኘ መሆኑን መዘገባቸው በሪያድ ላይ ዓለም አቀፍ ተቃውሞን አስከትሎባታል፡፡