የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ወደ ተከታዩ ዙር ማለፍ ቻለ
አርትስ ስፖርት 12/03/2011
ወጣት ብሔራሔዊ ቡድኑ በመጭው የፈረንጆች ዓመት በግብፅ አስተናጋጅት ለሚካሄደው የአፍሪካ ከ23 ዓመት በታች ዋንጫ ለመሳተፍ የመጀመሪያ ማጣሪያ፤ የመልስ ጨዋታውን ትናንት ከሶማሊያ አቻው ጋር አካሂዷል፡፡ ሶማሊያ ላይ ባለው አለመረጋጋት ምክንያት ጅቡቲ ላይ በተካሄደ የመልስ ግጥሚያ ሶማሊያ 1 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፋለች፡፡ ከሳምንት በፊት አዲስ አበባ ላይ ኢትዮጵያ 4 ለ 0 በሆነ ሰፊ ውጤት ማሸነፏ የሚታወስ ሲሆን በአጠቃላይ የ4 ለ 1 ውጤት የበላይነት ወደ ሁለተኛው ዙር ማለፍ ችላለች፡፡ የኢትዮጵያ የተጫዋቾች ስብስብ ግን አሁንም ከዕድሜ ተገቢነት ጋር በተያያዘ ጥያቄ እየተነሳበት ይገኛል፡፡
በቀጣይ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በሁለተኛው ዙር የመጀመሪያውን ማጣሪያ መጋቢት 11/2011 ዓ/ም አዲስ አበባ ላይ ከ ማሊ የ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ጋር የሚያካሂድ ይሆናል፡፡