ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ እንደ አዲስ ለሚደራጀው የምርጫ አስፈጻሚ ተቋም አመራርነት ታጭተዋል ተባለ
አርትስ 12/03/2011
ወ/ሪት ብርቱካን በመንግስት ጥሪ የተደረገላቸው በአሁኑ ወቅት ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ተብሎለሚጠራው ተቋም ነው ተብሏል።
ሪፖርተር ጋዜጣ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ምንጮቹን ጠቅሶ እንደዘገበው በቅርቡ ስያሜውንና አጠቃላይ አደረጃጀቱን በማሻሻል ሙሉ በሙሉ ገለልተኛ ሆኖ ይቋቋማል ተብሎ የሚጠበቀውን ይህንኑ አገር አቀፍ ምርጫ አስፈጻሚ ተቋም ወይዘሪት ብርቱካን ይመሩታል ተብሎ ይታሰባል።
ጋዜጣው አንዳለው ወይዘሪት ብርቱካን ሰሞኑን ጥቁር አንበሳ አካባቢ በሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ቅጥር ግቢ የታዩ ሲሆን እዚያ መገኘታቸውም የተቋሙን አደረጃጀትና ሁኔታዎች በግላቸው ለማጤን ያደረጉት ጉብኝት ሊሆን ይችላል ብሏል ።