Ethiopia

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ለኢትዮጵያ የ960 ሚሊዮን ብር ብድር ሊሰጥ ነው

የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ለኢትዮጵያ የ960 ሚሊዮን ብር ብድር ሊሰጥ ነው

አርትስ 14/03/2011

ኢትዮጵያ ከአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ጋር የ960 ሚሊዮን ብር ብድር ስምምነት ተፈራርማለች፡፡

ብድሩ በገጠርና በከተማ በጥቃቅንና አንስተኛ ዘርፍ የተሰማሩ ሴት ስራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ እንደሚውል ተገልጿል፡፡

ስምምነቱን የገንዘብ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ እና የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ፕሬዝዳንት ወርነር ሆየር በሸራተን አዲስ ሆቴል ተፈራርመዋል፡፡

እኛ ሁሉን አቀፍ ፕሮጀክት ላይ መስራት ነው የምንፈልገው ያሉት ዶ/ር ወርነር ኢትዮጵያ ለጾታ እኩልነት እየሰራች መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

አካታችና ቀጣይነት ያለው እድገት ማስመዝገብ የሚቻልበትን ሁኔታን ለማገዝ በማሰብ የብድር ስምምነቱን እንደፈረሙም ተናግረዋል፡፡

የገንዘብ ሚንስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የመንግስት የቢዝነስ ተቋማትን ሙሉ በሙሉ ይሁን በከፊል ለግሉ ዘርፍ በማዘዋወር ላይ መሆኑዋን ተናግረዋል፡፡

እንደ ሀገር ለግሉ ዘርፍ በቂ ብድር የማቅረብ ችግር እንዳለም ጠቁመዋል፡፡
አቶ አህመድ ሺዴ የአውሮፓ ኢንቨስትመንት ባንክ ወደፊትም ለኢትዮጵያ የሚያደርገውን ድጋፍና አጋርነት አጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami