አርትስ 14/03/2011
የዚምባብዌ ፋይናንስ ሚኒስትር ምቱሊ ንኩምቤ ፕሬዝዳንት ኤመርሰን ምናንጋግዋን ጨምሮ የሚኒስትሮችና ከፍተኛ ባለስልጣናት ደመወዝ በ5 በመቶ እንደተቀነሰ አስታውቀዋል፡፡
አፍሪካ ኒውስ እንደዘገበው የፋይናንስ ሚኒስትሩ ለፓርላማ ባቀረቡት ሪፖርት የደመወዝ ቅነሳው ዓላማ የመንግስት ወጭ ለመቀነስ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
የመንግስት ሰራተኞች ደመወዝ 90 በመቶ የሚሆነውን የዚምባብዌን ገቢ የሚጋራ ሲሆን ይህም ላለፉት 20 ዓመታት የሀገሪቱን ኢኮኖሚ ቁልቁል እነዲጓዝ አድርጎታ ነው የተባለው፡፡
የትምህርት ሚኒስትሩ ኦርባዲያ ሞዮ /Orbadiah Moyo/ አዲሱን ውሳኔ መቋቋም አለብን ምክንያቱም ሀገሪቱ የጤናውን ዘርፍ ጨምሮ በርካታ ችግሮች አሉባት ብለዋል፡፡
ለፓርላማ ቀርቦ ይሁንታን ያገኘው አዲሱ የደመወዝ ቅነሳ ከመጭው ጥር ወር ጀም ተግባተራዊ እንደሚሆንም ታውቋል፡፡
አሁን በሚደረገው የደመወዝ ወጭ ቅነሳ ዚምባብዌ በቀጣዩ የበጀት ዓትመት የ3.1 በመቶ ተጨማሪ እድገት እንደምታስመዘግብ ይጠበቃል ብለዋል የፋይናንስ ሚኒሰትሩ፡፡