Africa

አቡዳቢ ሱዳንን ከኳታር ጋር እንድታሸማግላት ጠየቀች

አርትስ 14/03/2011

የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች ከዶሀ ጋር እርቅ የመፍጠር ፍላጎት እንዳላትና ለዚህም ሁነኛ አስታራቂዋ  ካርቱም እንደሆነች ተናግራለች፡፡

ቁድስ ፕሬስ ስማቸው ያልተጠቀሰ የዶሀ ባለ ስልጣንን ጠቅሶ እንደዘገበው ኳታር ከገልፍ ሀገራት እንድትገለል ያደረገችኝ በዋናነት አቡዳቢ ናት ብላ ታምናለች፡፡

በዚህም የተነሳ የኳታር ባለስልጣናት ከተባበሩት አረብ ኢምሬቶች አቻዎቻቸው ጋር በአንድ ጠረጴዛ ተቀምጠው የመነጋገር ፍላጎት የላቸውም፡

በአንፃሩ ኳታር ከሳውዲ አረቢያ ጋር ግንኙነቷን ብትጀምር ቅር እንደማትሰኝ ትናገራለች፡፡ ይሁን እንጂ ሪያድ በጋዜጠኛ ጀማል ካሾጊ ጉዳይ ከገባችበት አጣብቂኝ እስክትወጣ ድረስ በትዕግስት መጠበቅ ግድ ሆኖባታል፡፡

ሳውዲ አረቢያ፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች፣ ባህሬንና ግብፅ  እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር በ2017 ሽብርተኘትን ትደግፋለች በሚል ምክንያት ተባብረው ኳታር ላይ ማዕቀብ መጣላቸው ይታወሳል፡፡

Show More

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button
Close
Close
Close Bitnami banner
Bitnami