አርትስ ስፖርት 17/03/2011
ቱር ኢትዮ_ኤርትራ የብስክሌት ውድድር፤ የሰላም፣ የአንድነትና የአብሮነት ተጓዦች ከፎንተኒናእስከ ደሴ ያለውን ፈታኝ፣ ዳገታማ፣ ጠመዝማዛ 39 ኪ.ሎ ሜትሩን ጋልበው ደሴ ከተማገብተዋል።
የብስክሌት ጋላቢዎች ደሴ ሲገቡ ከፍተኛ አቀባበል በከተማ አስተዳደሩ እና ነዋሪዎችተደርጎላቸዋል ። በነገው ዕለት ከደሴ ከተማ 199 ኪ.ሜ በመኪና አላማጣ ድረስ ከተጓዙበኃላ 19 ኪ.ሎ ሜትር ከአላማጣ አስከ ኮረም ይጋልባሉ ተብሎ ይጠበቃል ።
ከአዲስ አበባ ጀምሮ ብስክሌተኞቹና ልዑካኑ በሰላም ተግባራቸውን እያከናወኑና በየደረሱበትከተማ ደማቅ አቀባበል እየተደረገላቸው መሆኑን አቶ ረዘነ በየነ የአዲስ አበባ ብስክሌትፌዴሬሽን ፕሬዝዳንትና የልዑኩ የበላይ አስተባባሪ ገልፀውልኛል ሲሉ የአዲስ አበባ ወጣቶችናስፖርት ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት አስታውቋል ።